Notice
ለዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ
በኢ.ፌ.ድ.ሪ ንግድ ህግ አንቀፅ 366(1)፣ 367(1 እና 2)፣ አንቀፅ 370 አንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ አንቀፅ 13(2) መሠረት የዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሠዓት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው ዲ ሊዮፖል (de leopol) ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በመሆኑም የተከበራችሁ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ ጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1.ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1. የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 3 በተለምዶ አትላስ አካባቢ ባለው የማህበሩ ህንፃ፣ ድረ ገፅ፡ www.abayinsurance.com
1.2 የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡- የንግድ ምዝገባ ቁጥር MT/AA/2/0011521/2004፣ የመድን ሥራ ፈቃድ ቁጥር 015/10
1.3. የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- ብር 1,000,000,000
1.4. የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- ብር 791,887,000
2. የ15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1. የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ፣
2.2. እ.ኤ.አ በ2024/25 የተፈፀሙ የአክሲዮን ሽያጮች እና አክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅ፣
2.3.እ.ኤ.አ የ2024/25 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፣
2.4.እ.ኤ.አ የ2024/25 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፣
2.5.እ.ኤ.አ የ2024/25 የባለአክሲዮኖችን የትርፍ ድርሻ ክፍፍል መወሰን፣
2.6.የውጭ ኦዲተር ባቀረበው ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ጥያቄ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
2.7. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2024/25 ዓመታዊ የሥራ ዋጋና የ2025/26 ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያን መወሰን፣
2.8. ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚያገለግሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፡፡
1. ማሳሰቢያ
1.1. በጉባዔው ላይ መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሠነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ህግ አንቀፅ 377 መሰረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሶስት ቀን በፊት በማህበሩ ፀሐፊ ቢሮ ወይም አቅራቢያችሁ በሚገኙ የኩባንያው ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የውክልና ቅፅ እንዲሞሉና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተወካይ ለመሆንና ድምፅ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናስገነዝባለን፡፡
1.2. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆኖ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላችሁ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ ያለብዎት መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
የዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ
ለዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ፤
ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሚያካሂደው 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ይካሄዳል፡፡ ለዚሁ ዓላማ የተቋቋመው የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ከባለአክሲዮኖች ጥቆማ በመሰብሰብ መመሪያው ላይ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት 18 ዕጩ ተወዳዳሪዎቸን በመለየት ከዚህ እንደሚከተለው የመጨረሻ ዝርዝር ማቅረቡን በማክበር እንገልፃለን፡፡
ለዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የዴሬክተሮች ቦርድ አባልነት ምርጫ የመጨረሻ 18 ዕጩ ዝርዝር ለማግኘት ማስፈጠሪውን ያጫኑ። https://abayinsurance.com/wp-content/uploads/2025/12/Notice-of-nominee-list-1.pdf
የዳሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ!
ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ
Branch Opening
Congratulation!
We are thrilled to announce our 45th Branch Opening in Butajira city. Our new branch features a modern and inviting design, with a focus on providing a personalized and efficient experience. Abay Insurance! Your Peace of Mind!
End of a Budget Year
Celebrating the End of a Budget Year and Looking Ahead
As we conclude another budget year, our CEO, Yohannes Zewdie, extends his heartfelt congratulations to the entire team. “Your hard work and dedication have been instrumental in achieving our goals and setting a strong foundation for the upcoming budget year,” CEO said.
He emphasized the importance of continuing this momentum as we embark on the new budget year with renewed energy and focus. “Together, we will reach even greater heights,” he added.
Let’s celebrate our achievements and look forward to another year of success.CEO
Our 44 Branch Opening
Congratulation!
We are opening several new branches aimed at expanding services and enhancing customer satisfaction. Our 44th branch, Kolfe-18 Mazoria is opened to you!